ትውልዱ እየተገበረ ባለው የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህል የሴቶች አደረጃጀት አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
“በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ በወሰን ተሻጋሪ በጎ አገልግሎት በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ የችግኝ ተከላና የአቅመ ደካማ እናት ቤት ግንባታን አስጀምረዋል።
የአሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ስመኝ ተስፋዬ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በጎ ተግባር አንድነትና የእርስ በርስ ግንኙነትን በማጠናከር ለሌሎች የምንደርስበት አንዱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢንሼቲቭ መሆኑን አንስተው የባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ስላደረጉት ሰው ተኮር ተግባር አመስግነዋል።
በጎ ተግባር በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም ዋጋ ስላለው አቅመ ደካማ እናቶችን መርዳት የሁሉም ተግባር ሊሆን ይገባል ያሉት የባስኬቶ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አስቴር ሰነቀ ናቸው።
የባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መብቴ ግሮ እንዳስረዱት፤ “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ትውልዱ እየተገበረ ባለው የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህል በሴቶች ክንፍ የተከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሲሳይ ጋልሺ፤ የባስኬቶ ብሄር ከወንድም አሪ ሕዝብ ጋር የጠበቀ ቁርኝት መኖሩን ተናግረው ይህን አንድነትና ወንድማማችነትን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
በሴቶች የወሰን ተሻጋሪ በጎ አገልግሎት ቤት የተገነባላቸው እናትም በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልፀው ምስጋናቸውንም አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
መረጃ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለጸ
ተዓማኒና ወቅቱን የጠበቀ መረጃ ለሀገራዊ ውሳኔ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገለፀ
ለጠቅላላ አገራዊ ምርት ግምት መሠረታዊ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ለሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ