አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ ወደ ፍፃሜ አለፈች

በ2025ቱ የቶኪዮ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 1500 ሜትር ከኢትዮጵያ ብቸኛ ተወካይ የሆነችው አትሌት ፍሬወይኒ ወደ ፍፃሜው ማለፍ ችላለች።

በመጀመሪያው ምድብ ሆና የግማሽ ፍፃሜ ውድድሯን ያከናወነችው አትሌቷ ምንም እንኳን በውድድሩ መኃል ተደናቅፋ ወድቃ የነበረ ቢሆንም ከወደቀችበት ተነስታ በመሮጥ ውድድሯን በሶስተኝነት አጠናቃ ወደ ፍፃሜው መሻገሯን አረጋግጣለች።

የ1500 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ውድድር የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ላይ የሚካሄድ ይሆናል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ