የ10 ሺህ ሜትር ወንዶች የፍፃሜ ውድድር ከደቂቃዎች በኋላ ይካሄዳል

በጃፓን ቶኪዮ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺህ ሜትር ወንዶች የፍፃሜ ውድድር ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ይከናወናል።

ኢትዮጵያ ሜዳልያ ለማሸነፍ በምትጠበቅበት ርቀት በሦስት አትሌቶች ትወከላለች።

አትሌት ሰለሞን ባረጋ፣ አትሌት በሪሁን አረጋዊ እና አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ኢትዮጵያን በመወከል ከ14 ዓመታት በኋላ በሻምፒዮናው ለሀገራቸው የወርቅ ሜዳልያ ለማምጣት የሚወዳደሩ አትሌቶች ናቸው።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ለመጨረሻ ጊዜ ወርቅ ያገኘችው እንደ አውሮፓውያኑ በ2011 በዴጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአትሌት ኢብራሂም ጄላን አማክኝነት መሆኑ አይዘነጋም።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ