ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለአሸናፊነት የሚጠበቁበት የሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለአሸናፊነት የሚጠበቁበት የሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለሜዳልያ አሸናፊነት የሚጠበቁበት የሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር በዛሬው ዕለት ከቀኑ 9:30 ይካሄዳል።

በውድድሩ ኢትዮጵያ በአራት አትሌቶች ትወከላለች።

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ፣ አትሌት ፎትየን ተስፋይ እና አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ ኢትዮጵያን በመወከል ይወዳደራሉ።

በተጨማሪ በሻምፒዮናው በመክፈቻ ቀኑ ውሎ የ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ወንዶች 6:05 እና በ1500 ሜትር የሴቶች ውድድር ከቀኑ 7:50 የማጣሪያ ውድድሮች ይከናወናሉ።

ዘጋቢ: ሙሉቀን ባሳ