የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በቦንጋ ከተማ የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት አካል የሆነውን እና 2.34 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የኮሪደር ልማት ጎበኙ፡፡
በከተማው እየተከናወነ የሚገኘው ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ የተሻለ ደረጃ ላይ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም አንስተዋል።
ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ከ75 በመቶ በላይ መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን ጨምሮ የሳይት ማፅዳትና ድልድዮችን የማጠናቀቁ ስራ እንደሚከናወን ተመላክቷል፡፡
በጉብኝቱ የክልሉ፣ የካፋ ዞንና የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ዳንኤል መኩሪያ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
የሸካቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ማሽቃሬ ባሮ” እየተከበረ ነው
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቱሪዝም ቢሮ 2018 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ግምገማ እና 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እያካሄደ ይገኛል
የአርሶአደር ማሰልጠኛ ማዕከላት ለግብርና ቴክኖሎጂ ሽግግርና ምርታማነት ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ሊጠናከሩ እንደሚገባ ተገለፀ