ማቲያስ ኩንኛ ከደርቢው ጨዋታ ውጪ ሆነ

ማቲያስ ኩንኛ ከደርቢው ጨዋታ ውጪ ሆነ

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ማቲያስ በመጪው ዕሁድ በማንቹሪያን ደርቢ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ከሚያከናውነው ወሳኝ ጨዋታ ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

ማቲያስ ኩንኛ በፕሪሚዬር ሊጉ የ3ኛ ሳምንት መርሐግብር ከበርንሌይ ጋር በተካሄደው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ጉዳት በማስተናገዱ ምክንያት ተቀይሮ ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል።

ተጫዋቹ ከጉዳቱ ባለማገገሙ ከለቡ የፊታችን ዕሁድ በሚያከናውነው ተጠባቂ ጨዋታ የኩኛን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ማሰን ማውንት እና ዲያጎ ዳሎትም እንዲሁ በጉዳት ምክንያት እንደማይኖሩ አሰልጣኙ ገልፀዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ከነገ በስቲያ ወደ ኤቲሐድ አቅንቶ የከተማ ባላንጣውን ማንቸስተር ሲቲን ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ የሚገጥም ይሆናል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ