ካርሎስ አልካሬዝ የዓለማችን ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ሆነ
ስፔናዊው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ካርሎስ አልካሬዝ የዩኤስ ኦፕን ውድድርን ማሸነፉን ተከትሎ የዓለማችን ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ደረጃን መያዝ ችሏል።
ካርሎስ አልካሬዝ በዩኤስ ኦፕን የሜዳ ቴኒስ ፍፃሜ አራት ዙር በፈጀው ውድድር ጣሊያናዊውን ጃኒክ ሲነርን 6 – 3፣ 3 – 6፣ 6 – 1 እና 6 – 4 በማሸነፍ 6ኛውን የግራንድ ስላም በእጁ አስገብቷል።
የ22 ዓመቱ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች የግራንድ ስላምን 6 ጊዜ በማሸነፍ በዕድሜ ትንሹ ተወዳዳሪ ሆኗል።
ካርሎስ አልካሬዝ ከዓለማችን ዋና ዋና የሜዳ ቴኒስ ውድድሮች መካከል የፍሬንች ኦፕን፣ ዊምብልደንን እና ዩኤስ ኦፕንን እያንዳንዳቸውን ሁለት ጊዜ አሸናፊም ሆኗል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የኅብር ቀንን ስናከብር ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጎልበት ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ ከተማ ጌታነህ ከበደን አስፈረመ
1 ሺህ 47 ማልያዎችን የሰበሰበው የሊቨርፑሉ ደጋፊ