የኅብር ቀን ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የኣሪ ዞን አስተዳደር ገለጸ

የኅብር ቀን ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የኣሪ ዞን አስተዳደር ገለጸ

ሀዋሳ፡ ጷጉሜን 2/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኅብር ቀን ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ሲሉ የኣሪ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ታሪካዊ እና የተፈጥሮ እሴቶች ያሏት ትልቅ ሀገር ነች ያሉት የኣሪ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ስመኝ ተስፋዬ፥ ጷጉሜን 2 የኅብር ቀን ስናከብር ኢትዮጵያ ያሏት ብሔር ብሔረሰቦች ብዝሃ ባህልና ቋንቋ፣ በርካታ የጋራ የሆኑ ቱውፊቶችን ደምቆ እንዲቀጥል የቀኑ መከበር ብዙ ትርጉም አለው ብለዋል።

የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ በበኩላቸው “ብዝሃነት ለኢትዮጵያ ጌጥ” መሆኑን ጠቁመው፥ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለህብር ቀን ተምሳሌት ናት ብለዋል።

ልዩነቶቻችንን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመን የጋራ እሴቶቻችንን አጉልተን ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና እንድትሸጋገር እጅ ለእጅ ተያይዘን ልንሠራ ይገባናል ብለዋል።

ዛሬ ላይ በህብረ-ብሔራዊ አንድነት የምንፈፅማቸው ሁሉ አቀፍ የልማት ተግባራት የነገ ትውልድ የበለፀገች ሀገርን እንዲረከቡ ያደርጋልና ሁላችን ተግተን እንሥራ ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።

በመድረኩ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት በማድረግ የዓመት በዓል የሚሆን የምግብ ዘይትና ዱቄት በድጋፍ መልክ አበርክተዋል።

እንደ ሀገር በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎችና ቀድሞ የነበሩ ተግዳሮች በሰነድ መልክ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።

በመድረኩ የዞንንና የወረዳ አመራሮች፣ እንዲሁም የከተማ አስተዳደርና ሌሎች ተገኝተው የኅብር ቀንን “ብዝሃነት ለኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መርህ ሐሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል ።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን