የህብር ቀን “ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ሐሣብ በማዕከላዊ ኢትዮያውያ ክልል ሣጃ ክላስተር እየተከበረ ነው
የጳጉሜን ቀናትን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት የተለያዩ ስያሜዎችን በመሠየም ልዩ ትኩረት ሠጥቶ እየሠራ ነው ።
ዘንድሮም ጰጉሜ ሁለትን የሕብር ቀን በማለት ብሔራዊ አንድነትን አብሮነትንና ብዙ ሆነው በአንድ ሀሣብ ማደግን መሠረት በማድረግ እየተከበረ ይገኛል።
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሣጃ ክላስተር ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የክላስተሩ የዞኑ እና ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የሣጃ ዙሪያ አመራሮችና ሠራተኞች በወንድማማችች አደባባይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ጉዞ በማድረግ የሣጃ ከተማን የልማት ሥራዎች ጉብኝት ተደርገዋል።
ቀኑን አስመልክቶ የተለያዩ ባህላዊ ቁሣቁሦች ኤግዝቢሽን እና የደም ልገሣ መርሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ማሙዬ ፊጣ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ከተስፋ ወደ ሚጨበጥ ብርሀን ለመሻገር በተሰሩ ተግባራት ውጤት ማምጣት መቻሉ ተገለጸ
የኅብር ቀን ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የኣሪ ዞን አስተዳደር ገለጸ
የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ስራው ተጠናቆ ለምረቃ መድረሱ እንዳስደሰታቸው በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ