አርሰናል ማክስ ዶውማንን በሻምፒዮንስ ሊጉ ስብስብ አካተተ
የእንግሊዙ ክለብ አርሰናል ታዳጊውን የፊት መስመር ተጫዋች ማክስ ዳውማንን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ስብስቡ ማካተቱ ይፋ ሆኗል።
የ15 ዓመቱ ተጫዋች የሰሜን ለንደኑ ክለብ ለአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በላከው የዋናው ቡድን 23 ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።
በቀጣይ ህዳር ወር ላይ ወር 16 ዓመት የሚሞላው ማክስ ዶውማን ከዚያ ቀደም ብሎ በሻምፒዮንስ ሊጉ ተሰልፎ የሚጫወት ከሆነ በውድድሩ ታሪክ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች ይሆናል።
አሁን ላይ የዚህ ታሪክ ባለቤት ካሜሮናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ዩሱፋ ሙኮኮ መሆኑ ይታወቃል።
የሚኬል አርቴታው ቡድን በአንፃሩ በጉዳት ምክንያት ለ7 ወራት ከሜዳ ርቆ የቆየውን ጋብርኤል ጄሱስን በሻምፒዮንስ ሊጉ ስብስብ ውስጥ አለማካተቱ ተገልጿል።
አርሰናል በ2025/26 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የውድድር ዘመን በመጀመሪያው ዙር በሜዳው ከባየር ሙኒክ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ኦሎፒያኮስ፣ ካራይት አልማቲ እንዲሁም ከሜዳው ውጪ ደግሞ ከኢንተር ሚላን፣ ክለብ ብሩጅ፣ ስላቪያ ብራህ እና አትሌቲክ ቢልባኦ ጋር መደልደሉ ይታወቃል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሀዋሳ ከተማ ጌታነህ ከበደን አስፈረመ
1 ሺህ 47 ማልያዎችን የሰበሰበው የሊቨርፑሉ ደጋፊ
አትሌቲኮ ሚኒዬሮ ሆርጌ ሳምፖሊን በድጋሚ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ