አትሌቲኮ ሚኒዬሮ ሆርጌ ሳምፖሊን በድጋሚ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አትሌቲኮ ሚኒዬሮ ሆርጌ ሳምፖሊን በድጋሚ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

የብራዚሉ እግር ኳስ ክለብ አትሌቲኮ ሚኒዬሮ የቀድሞ አሰልጣኙን ሆርጌ ሳምፖሊን በድጋሚ መሾሙን አስታውቋል።

ከአሰልጣኝ ማርቲን አንሰልሚኒ ጋር በትላንትናው ዕለት የተለያየ ሚኒዬሮ ከአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ጋር እስከ 2027 ድረስ የሚያቆየውን ውል መፈራረሙን ገልጿል።

የ65 ዓመቱ አሰልጣኝ ሆርጊ ሳምፖሊ በ2020 ከጋሎዎች ሀላፊነት መሰናበታቸው ይታወሳል።

አትሌቲኮ ሚኒዬሮ በዚህ ዓመት በብራዚል ሴሪኣ በ24 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በአሰልጣኝነት ዘመናቸው ከ700 በላይ ጨዋታዎችን በሀላፊነት የመሩት ሆርጌ ሳምፖሊ ከዚህ ቀደም ሲቪያን፣ ኦሎምፒክ ማርሴን፣ ስታድ ሬንስን እና ሳንቶስን ማሰልጠናቸው አይዘነጋም።

በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ደግሞ ሁለቱን የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ቺሊን እና አርጄንቲናን በሀላፊነት መርተዋል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ