ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ

ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ

ማንቸስተር ዩናይትድ የሮያል አንትወርፑን ግብ ጠባቂ ሴኔ ላሜንስ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል።

የዚህ ውድድር ዓመት አጀማመር ያላማረለት ማንቸስተር ዩናይትድ ቤልጂየማዊውን ግብ ጠባቂ በ21 ሚልዮን ዩሮ እና ተጨማሪ ክፍያ ለማስፈረም መስማማቱን የፋብሪዚዮ ሮማኖ መረጃ አመላክቷል።

የ23 ዓመቱ ግብ ጠባቂ በዛሬው ዕለት የጤና ምርመራው ካጠናቀቀ በኋላ የ5 ዓመት ኮንትራት ከቀያይ ሰይጣኖች ጋር ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።

ሴኔ ላሜንስ ባለፈው የውድድር ዓመት በ30 የቤልጅየም ፕሮ ሊግ ጨዋታዎች የተሰለፈ ሲሆን በ7 መርሐግብሮች ጎል ሳይቆጠርበት ከሜዳ ወጥቷል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ