ሪያል ቤቲስ በአንቶኒ ዝውውር ከስምምነት ላይ ደረሰ
የእስፔኑ ክለብ ሪያል ቤቲስ አንቶኔሊ ዶሳንቶስን ከማንቸስተር ዩናይትድ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል።
የአንዳሉሲያው ክለብ ከቀናት በፊት ብራዚላዊውን ተጫዋች ለማስፈረም በመርህ ደረጃ ከተስማማ በኋላ የአንቶኒን ቀሪ የደመወዝ ክፍያ መሸፈን እንደማይፈልጉ ገልፀው ከዝውውሩ መውጣታቸውን ገልፀው ነበር።
አሁን ላይ ግን ሁለቱ ክለቦች በአንቶኒ ዝውውር የነበራቸውን ልዩነት አጥበው ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተረጋግጧል።
የአሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒው ቡድን ለ25 ዓመቱ ተጫዋች ዝውውር 25 ሚሊዮን ዩሮ እና በቀጣይ የሚታከል 5 ሚሊዮን ዩሮ ገንዘብ ለመክፈል ተስማምቷል።
በተጨማሪም ከተጫዋቹ የወደፊት ሽያጭ ማንቸስተር ዩናይትድ 50 በመቶ ክፍያ እንዲያገኝ የሚያስችል ስምምነትም በዝውውሩ መካተቱን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
አንቶኒ ዶሳንቶስ ከሌሎች ክለቦች የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ሪያል ቤትስን ብቻ መቀላቀል ምርጫው ሆኗል።
እንደ አውሮፓውያኑ በ2022 በማንቸስተር ዩናይትድ ታሪክ 2ኛው ውዱ ፈራሚ ሆኖ ወደ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ ማምራቱ ይታወሳል።
በቀያይ ሰይጣኖች ቤትም 96 ጨዋታዎችን አከናውኖ 12 ግቦችን አስቆጥሯል።
በማንቸስተር ዩናይትድ ማልያ የመጀመሪያ ጎሉን አርሰናል ላይ ያስቆጠረው አንቶኒ ወደ እንግሊዝ ሲመጣ ብዙ በላቀ ደረጃ ይጫወታል ተብሎ ቢጠበቅም የእንግሊዝ ቆይታው ያለስኬት ተጠናቋል።
የ25 ዓመቱ የመስመር ተጫዋች በጥር የዝውውር መስኮት ለሪያል ቤትስ በውሰት መጫወቱ ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሊቨርፑል አሌክሳንደር ኢዛክን ክብረወሰን በሆነ ሒሳብ ለማስፈረም ተስማማ
ማንቸስተር ሲቲ በአዲሱ የውድድር ዓመት 2ኛ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል