ሊቨርፑል አሌክሳንደር ኢዛክን ክብረወሰን በሆነ ሒሳብ ለማስፈረም ተስማማ

ሊቨርፑል አሌክሳንደር ኢዛክን ክብረወሰን በሆነ ሒሳብ ለማስፈረም ተስማማ

የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል አሌክሳንደር ኢዛክን ከኒውካስል ዩናይትድ በዩናይትድ ኪንግደም ክብረወሰን በሆነ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል።

የመርሲሳይዱ ክለብ ለስውድናዊ የፊት መስመር ተጫዋቾች ክብረወሰን የሆነ 130 ሚሊዮን ፓውንድ ለኒውካስል ለመክፈል መስማማቱን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

አሌክሳንደር ኢዛክ በሊቨርፑል የሚያቆየውን የ6 ዓመት ኮንትራት የሚፈርም ሲሆን ዝውውሩን ለማጠናቀቅ የጤና ምርመራ እንደሚያከናውን ተገልጿል።

በ2022 ከሪያል ሶሴዳድ ወደ ኒውካስል የተዛወረው ኢዛክ በማግፓይሶቹ ቤት በነበረው ቆይታ በ109 ጨዋታዎች 62 ጎሎችን ሲያስቆጥር 11 ግብ የሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።

በፕሪሚዬር ሊጉ ብቻ 54 ጎሎችን በስሙ ያስመዘገበው ተጫዋቹ ኒውካስል ባለፈው ዓመት በካራባው ካፕ ፍፃሜ ሊቨርፑልን በማሸነፍ ከ70 ዓመታት በኋላ ዋንጫን ሲያነሳ አስተዋጽኦው ከፍተኛ እንደነበር አይዘነጋም።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ