ጄሚ ቫርዲ ወደ ጣሊያን ሴሪኣ ሊያቀና ነው
በሌስተር ሲቲ ቤት ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ከ13 ዓመታት በኋላ ከእንግሊዙ ክለብ ጋር የተለያየው ጄሚ ቫርዲ ለጣሊያኑ ክለብ ክሪሞንሴ በነፃ ለመፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል።
የቀበሮዎቹ ሌጀንድ ዘንድሮ ወደ ሴሪኣ ካደገው ክሬሞንሴ ጋር የ1 ዓመት ውል ለመፈራረም መስማማቱን የፋብሪዚዮ ሮማኖ መረጃ አመላክቷል።
ክለቡ በቀጣይ ዓመት በሴሪያው መቆየት የሚችል ከሆነ ቫርዲ ለተጨማሪ አንድ አመት በክለቡ ኮንትራቱን ማራዘም የሚችልበት አማራጭ ተቀምጦለታል።
የ38 ዓመቱ አንጋፋ በቀድሞው የአርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ ዝነኛ ተጫዋች ሮቨን ቫንፔርሲ ከሚሰለጥነው ፌይኖርድ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ወደ ጎን ማለቱ ተነግሯል።
እንግሊዛዊው የጎል ጨራሽ እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 ከሌስተር ሲቲ ጋር የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫን ማንሳቱ ይታወሳል።
በሌስተር ሲቲ በነበረው ቆይታም 500 ጨዋታዎችን በማከናወን 200 ጎሎችን በማስቆጠር እና 71 ለግብ የሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል የክለቡ የምንጊዜም ከፍተኛው ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ማንቸስተር ሲቲ በአዲሱ የውድድር ዓመት 2ኛ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል
ሊቨርፑል ከአርሰናል ከሰዓታት በኋላ ወሳኝ ግጥሚያ ያካሂዳሉ