የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ መምሪያ ከዋቸሞ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ከተለያዩ ተቋማት ለተወጣጡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 07/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ስልጠናው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ(IT) ባለሙያዎችን አቅም ከማሳደጉም በተጨማሪ በኢኖቬሺን፣ በኔትወርኪንግ፣ በኮምፒውተር፣ በፈጠራ ሥራ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የዋቸሞ ዩንቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፀደቀ ላምቦሬ ለሰልጣኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለሀገር ግንባታ እድገት ያለው ፋይዳ የላቀ ነው ብለዋል።
በቴክኖሎጂ በመታገዝ ውስብስብ የሆኑ የዓለም ችግሮችን በተገቢ መፍታት እንደሚቻልም ዶክተር ፀደቀ አመላክተዋል።
የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት አኑሎ በበኩላቸው፥ ሀገርን ለማበልፀግ በቴክኖሎጂ የበለፀጉ ዜጎች እንደሚያስፈልጉ ገልጸዋል።
የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ ዘርፍ ያለው ፋይዳ የጎላ እንደሆነም ጠቁመዋል::
በስልጠናው ከ60 በላይ ሰልጠኞች ከተለያዩ ተቋማት እየተሰተፋ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት በኢኖቬሺን፣ በኔትወርክንግና ኮምፒዩተር ጥገና እንዲሁም በፈጠራ ሥራ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ሰልጠኞች ስልጠናው ለራስና ለሚሠሩባቸው አካባቢ ማህበረሰብ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖራቸው ገልጸው፥ በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
በርካቶችን ከድካም የሚታደግ የፈጠራ ውጤት
የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሻሻል ምርታማነት እንዲጨምር የቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ተጨባጭ ለውጥ እንድናስመዘግብ ረድቶናል – በቤንች ሸኮ ዞን የሸይ ቤንች ወረዳ አርሶአደሮች
“ከቆቦ ዛፍ የተሽከርካሪ ነዳጅን መፍጠር የቻለው” – ወጣት ታሪኩ አዳነ