ሊቨርፑል ለአሌክሳንደር አይዛክ በድጋሚ የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርብ ነው
ሀዋሳ: ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል አሌክሳንደር አይዛክን ለማስፈረም በድጋሚ ለኒውካስል ዩናይትድ ጥያቄ ለማቅረብ መዘጋጀቱ ተገለጸ።
ከሶስት ሳምንታት በፊት አሌክሳንደር ኢሳክን ለማስፈረም 110 ሚልየን ፓውንድ አቅርቦ ውድቅ የሆነበት ሊቨርፑል የዝውውር መስኮቱ የፊታችን ሰኞ ከመዘጋቱ አስቀድሞ ተጨዋቹን ለማስፈረም የእንግሊዝ ሪከርድ የሆነ የተሻሻለ የዝውውር ለማቅረብ መሰናዳቱን ዘ ቴግራፍ አስነብቧል።
ምንም እንኳን ኒውካስል በሲውዲናዊው አጥቂ ላይ የ150 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ ቢለጥፍበትም የመርሲሳይዱ ክለብ የተሻሻለ 130 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ ይዞ ማግፓይሶቹን ለማነጋገር መወሰኑ ተሰምቷል።
የ25 አመቱ ስዊድናዊ አጥቂ ክለቡ እንዲለቀው ጫና ለማሳደር በኒውካስትል የቅድመ ውድድር ዝግጅትም ሆነ በክለቡ የፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች አለመሳተፉ ይታወቃል።
ኒውካስል ዩናይትድ የ 23ዓመቱ የፊት መስመር አጥቂ ኒክ ዎልተማዴን ከስቱትጋርት ለማስፈረም መስማማቱን ተከትሎ በአይሳክ ዝውውር ላይ መለሳለስ ማሳየቱንም ዘ ቴሌግራፍ አመላክቷል።
እንደ አውሮፓውያኑ በ2022 የኒውካስል ዩናይትድ ክብረወሰን በሆነ 63 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ከሪያል ሶሴዳድ የእንግሊዙን ክለብ የተቀላቀለው ኢሳክ ባለፈው የውድድር ዓመት በፕሪሚዬር ሊጉ 23 ጎሎችን በማስቆጠር ከሞሃመድ ሳላ በመቀጠል 2ኛው ኮከብ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
ዘጋዚ: ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሮድሪ እና ዳኒ ካርቭሃል ከ12 ወራት በኋላ ወደ ስፔን ብሔራዊ ቡድን ተመለሱ
አርሰናል የፒኤሮ ሂንካፔን ዝውውር ከማጠናቀቁ አስቀድሞ ሁለት ተከላካዮቹ ክለቡን ሊለቁ ነው
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ ከፌነርባቼ ሃላፊነት ተነሱ