አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ ከፌነርባቼ ሃላፊነት ተነሱ

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ ከፌነርባቼ ሃላፊነት ተነሱ

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ ከቱርኩ ክለብ ሃላፊነታቸው መነሳታቸውን ክለቡ አሳውቋል።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ክለቡን ወደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማሳለፍ አለመቻላቸው ለስንብታቸው ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

ፌነርባቼ ረቡዕ ዕለት ወደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሻገር ከቤኔፊካ ጋር ባከናወነው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ተረቶ ማለፍ ሳይችል መቅረቱ ይታወሳል።

የ62 ዓመቱ አሰልጣኝ ባለፈው ዓመት ነበር ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት የተረከቡት።

ጆዜ ሞሪኖ በቱርክ በስኬታማነት ከሚጠቀሱ ክለቦች መካከል አንዱ በሆነው የፌነርባቼ ቆይታቸው 62 ጨዋታዎችን የመሩ ሲሆን 37 አሸንፈው 14 ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት አጠናቀው 11 ጨዋታዎችን ደግሞ በሽንፈት አጠናቀዋል።

በክለብ ደረጃ የሚዘጋጁትን ሁሉንም የአውሮፓ መድረክ ውድድሮችን በማሸነፍ ብቸኛው አሰልጣኝ የሆኑት ጆዜ ሞሪኖ ከዚህ ቀደም ፖርቶን፣ ቼልሲን፣ ኢንተርሚላን፣ ሪያል ማድሪድን፣ ቶትንሃምን እና ሮማን ማሰልጠናቸው አይዘነጋም።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ