ዣቪ ሲሞንስ ወደ ቶትንሃም ለመዛወር የጤና ምርመራውን አጠናቀቀ

ዣቪ ሲሞንስ ወደ ቶትንሃም ለመዛወር የጤና ምርመራውን አጠናቀቀ

ኔዘርላንዳዊው የመሐል ስፍራ ተጫዋች ዣቪ ሲሞንስ ከአርቢ ሌፕዚግ ወደ ቶትንሃም ሆስትስፐርን ለመዛወር የጤና ምርመራውን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ለ22 ዓመቱ የጨዋታ አቀጣጣይ 60 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለመክፈል ከስምምነት ላይ መድረሱም ተነግሯል።

በሌላኛው የለንደን ከተማ ክለብ ቼልሲ በጥብቅ ይፈለግ የነበረው ሲሞንስ ለአሰልጣኝ ቶማስ ፍራንኩ ክለብ በዚህ ክረምት 4ኛው ፈራሚ በመሆን ስብስቡን ለመቀላቀል ተቃርቧል።

ከባርሴሎናው የላማሲያ አካዳሚ የተገኘው ዣቪ ሲሞንስ ከዚህ ቀደም ለፒኤስጂ እና ለፒኤስቪ ኤይንድሆቨን ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወቃል።

ዘጋቢ: ሙሉቀን ባሳ