አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ
ላለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት የቦሌ ክፍለ ከተማ እግርኳስ ክለብን በሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ሲመሩ የቆዩት አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሹመዋል።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በፖላንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2026 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ውድድሩን መስከረም ወር ላይ ይጀምራል።
ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድኑ በሁለተኛ ዙር ማጣርያ መስከረም 11 እና 18 የሚያከናውን ሲሆን አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ
ማንቸስተር ሲቲ ኤቨርተንን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆነ
ኖቲንግሃም ፎረስት አንጅ ፖስቴኮግሉን አሰናበተ