ሉካስ ቫዝኩዌዝ ወደ ባዬርሊቨርኩሰን ሊያመራ ነው
ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለው የውል ዘመን መጠናቀቁን ተከትሎ ከ10 ዓመታት በኋላ የሎስብላንኮዎቹን ቤት የለቀቀው ሉካስ ቫስኩዌዝ ወደ ጀርመኑ ክለብ ባዬርሊቨርኩሰን ለማቅናት መቃረቡ ተገልጿል።
ስፔናዊው ሁለገብ ተጫዋች የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃጉን ቡድን በሁለት ዓመት ውል ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ መድረሱን ማርካ አስነብቧል።
የ34 ዓመቱን ተጫዋች ለማስፈረም በዋናነት የስፔኑ ክለብ ዲፖርቲቮላካሩኛ ፍላጎት ቢያሳይም ከሪያል ማድሪድ ጋር በሌላ ክለብ ማልያ ላለመገናኘት ሲል የዝውውር ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል።
ሉካስ ቫዝኩዌዝ በሪያል ማድሪድ በቆየባቸው ጊዜያት ከ400 በላይ ጨዋታዎችን በማከናወን 5 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና 4 የስፔን ላሊጋ ዋንጫዎችን ጨምሮ 20 ዋንጫዎችን መሳም ችሏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ
ማንቸስተር ሲቲ ኤቨርተንን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆነ
ኖቲንግሃም ፎረስት አንጅ ፖስቴኮግሉን አሰናበተ