በደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ-ግብር ቤት የተገነባላቸዉ አካላት መደሰታቸውን ገለፁ
ወረዳዉ የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩን በማሻላ ቀበሌ አካሂዷል።
የማሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባሊንሠ እንዳሉት፤ በአጠቃላይ በወረዳው ሁሉም ቀበሌያት 116 ቤቶችን ሠርቶ ለአቅመ ደካሞች ለማስረከብ አቅዶ እየተራ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ በዚሁም ወደ አሥር ሚሊዮን ብር ለማዳን መታቀዱንም አስረድተዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ሀላፊ አቶ ያምላክስራ ናደው በበኩላቸው፤ አቅመ ደካሞችን የመደገፉ ስራ 960 ቤቶች እንደዞን እንደሚገነባና በዛሬዉ ዕለት በይፋ የተጀመረውን እስከ መጨረሻ ድረስ በማስቀጠል ባጭር ጊዜ በማጠናቀቅ አቅመ ደካሞቹን ተጠቃሚ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ቤት የተገነባላቸዉ አቅመ ደካሞች በወረዳዉ የማሻላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ሞትዞ ማቶ፣ ጊማቶ ግርማ እና አቶ ለማ ባልኦ በጋራ በሰጡት አስተያየት፤ መንግስትና ህዝብ በተባበረ ክንድ ላደረጉት ደጋፍ አመስግነው መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ዳኛቸዉ ደሴ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ሁሉ አቀፍ ድጋፍ የሚሹ አካላትን መርዳት የጥቂት አካላት ተግባር ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሥራ ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ
በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ የአንድ ጀምበር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተካሄደ
የዲላ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአንድ ጀምበር ቤቶች ግንባታ መርሐ ግብር በጎላ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ