የክረምት ዝናብን ተከትሎ ጎርፍ እና መሰል አደጋዎች በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ
ከጎርፍና መሰል አደጋዎች ባሻገር የከሰል እሳት አጠቃቀምም ላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ መምሪያው ጠቁሟል።
የዘንድሮው የክረምት ዝናብ ጠንከር ያለና ቀጣይነት ያለው መሆኑን የአየር ትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደርሶ በላይ፤ ሰሞኑን እየጣለ ባለው ዝናብ ምክንያት የመሬት መሸርሸር፣ ናዳ እና ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ልየታ በማድረግ ለአደጋ ተጋላጭ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ አካላት እንዲነሱ በማድረግ የቅድመ ጥንቃቄ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የውሃ ማፋሰሻ ቦዮችን በማፅዳትና ለጎርፍ መውረጃ ማዘጋጀት ይገባል ያሉት አቶ ደርሶ፤ ቆላማ አካባቢዎች ላይ ዝናብ ባይጥል እንኳ ወንዞች በደራሽ ዉሃ መሞላት ሊያጋጥም ስለሚችል ህፃናት ወደ ወንዝ እንዳይሄዱ መጠበቅ እንደሚገባም አስታውቀዋል።
አያይዘውም በክረምት ወራት ብርድን ለመከላከል ተብሎ ጥንቃቄ የጎደለው የከሰል እሳት መጠቀም ለሞት ስለሚዳርግ ከቤት ውጪ ከሰል ማቀጣጠል፣ በቤት ውስጥም በቂ አየር እንዲገባ በማድረግ ሊፈጠር ከሚችል አደጋ ራስን መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲሱ የካቢኔ ስብጥር ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗን በተግባር ያሳየ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ዕጩ የካቢኔ አባላት ከወትሮ በተለየ መንገድ ባለዕዳና ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ ማሳሰብ እወዳለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)