‎በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ የአንድ ጀምበር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተካሄደ

‎በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ የአንድ ጀምበር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተካሄደ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) “በጎነት ለአብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ ተካሂዷል፡፡

‎የሣላማጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህጉ ቅጣቱ ፤ የአንድ ጀምበር የአረጋዊያንና አቅመ ደካማ ቤት ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በገሮ ቀበሌ አካሂደዋል።

‎በ2017 ዓ.ም በክረምቱ ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር እንደ ወረዳ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ የሚገኙ ሲሆን ዛሬ የሚጀመረው የአንድ ጀምበር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በእጅጉ የሚያሳድግ ነው ብለዋል አስተዳዳሪው።

‎የሳላማጎ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠረት አስፋው እንደገለፁት፤ በክረምቱ ከሚከናወኑ መደበኛ ተግባራት ውጪ በወረዳው ባሉ ቀበሌያት ሁሉ 42 አዲስ ቤት ግንባታና 42 ዕድሳት በድምሩ 84 ቤቶችን በአንድ ቀን ጀንበር ለአቅመ ደካሞች ለመገንባት ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀዋል።

‎ኃላፊው አክለውም በንቅናቄ በሚሰራው ሥራ እንደ ወረዳ 8 ሺህ 580 በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ 18 ሺህ 850 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ 6 ሚሊየን 345 ሺህ 798 ብር ከመንግስት የሚወጣን ገንዘብ ለማዳን ታቅዶ እየተሠራ ነው።

‎የየቀበሌው ሊቀመናብርትና ወጣቶች መካከል አቶ ያረድ ወጽቶ፣ ገረሙ ዝጳን፣ ጳውሎስ ወቃሱ ወጣት ሳምኤል ባካንና ሌሎችም በአንድ ቀን ጀምበር ለሚከናወነው የአቅመ ደካማዎች ቤት ግንባታ በወጣቱ የነቃ ተሳትፎ እና በማህበረሰቡ በጎ ትብብር በጥሩ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

‎ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን