የዲላ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአንድ ጀምበር ቤቶች ግንባታ መርሐ ግብር በጎላ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ

የዲላ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአንድ ጀምበር ቤቶች ግንባታ መርሐ ግብር በጎላ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 19/2017 ዓ፣ም (ደሬቴድ) “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአንድ ጀንበር ቤቶች ግንባታ መርሐ ግብር በጎላ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል፡፡

‎መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር መስፍን ደምሴ፤ በከተማ አስተዳደሩ በአስር ቀበሌያት በአንድ ጀንበር ሶስት መቶ ቤቶች ለመገንባት ማቀዳቸውን ተናግረዋል።

‎የአንድ ጀምበር መርሀ ግብር ለ2 ሺህ 5 መቶ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ያሉት ከንቲባው፤ 10 ሚሊዮን ብር ከመንግስት ካዜና ይወጣ የነበረን ወጪ ለማዳን ዕቅድ መያዛቸውን አብራርተዋል።

‎ቤት ከመሠረታዊ ፍላጎቶች አንደኛውና ወሳኝ በመሆኑ ከክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ባሻገር በዲላ ከተማ ለነዋሪዎቹ በቂ ቤት የመገንባት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

‎የአንድ ጀንበር የቤቶች ግንባታ በንግድ፣ በመንግሥት ሰራተኞች፣ በወጣቶች እና በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማስተባበር እየተሠራ መሆኑን የዲላ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መንግስቱ ተክሌ ተናግረዋል።

‎የዲላ ከተማ አስተዳደር ስፖርት እና ወጣቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ አየለ፤ በጎነት ከራስ ለራስ የሚደረግ ተግባር በመሆኑ በከተማ አስተዳደር ወጣቶች በንቃት እየተሳተፉበት መሆናቸውን ገልጸዋል።

‎በከተማ አስተዳደሩ የአንዲዳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ማሙሽ ታሪኩ እና ወይዘሮ ትዕግስት ሰራዊት ከዚህ ቀደም ቤታቸው በማርጀቱ በዝናብ እና በጎርፍ ሲቸገሩ መቆየታቸውን አንስተው በተደረገው ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

‎ዘጋቢ: አሀዱ አሸናፊ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን