በገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አፈፃፀም ዙሪያ በሆሳዕና ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

በገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አፈፃፀም ዙሪያ በሆሳዕና ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አፈፃፀም ዙሪያ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከተረጂነት ለመውጣት በተቀናጀ ግብርና በተሰራው ስራ በተረጂዎች ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት መቻሉን የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ማዕረጉ ማቲዎስ አስታውቀዋል።

በክልሉ በ 35 ወረዳዎች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በተሰራው ልማታዊ ሴፍትኔት ከ 318 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸው አመላክተዋል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት ተቋሙ የገጠመውን የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተሰራው ስራ ህብረተሰቡ ወደ ምርታማነት መቀየር ተችሏል።

በቀጣይም የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና ከተረጂነት ለማውጣት በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

ዘጋቢ፡ ራሔል አሊ