አሊያንስ ኮሌጅ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን በማፍራት የሀገሪቱን ዕድገት ለማፋጠን የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታወቀ
ኮሌጁ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ800 በላይ ተማሪዎች በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።
የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አዲሱ አዳሙ (ዶ/ር)፤ ኮሌጁ ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ተሞክሮ የሚቀመርበት በመሆኑ በተቋሙ የተመረቁ ተማሪዎች ሥራ ፈላጊ ሳይሆኑ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።
የኮሌጁ ዲን አቶ ፋሲል ሰለሞን ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሀገር ወዳድና የሰላም ባለቤት እንዲሆኑ እንዲሁም ማህበረሰባቸውን በትጋት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።
ኮሌጁ በኢንፎርማቲክስና በቢዝነስ ፋኩልቲ በድግሪ መርሃ ግብር በመደበኛ፣ በማታና በርቀት 269 ተማሪዎችን እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በቢዝነስና አይሲቲ ዘርፍ 562 ተማሪዎችን በድምሩ 831 ተማሪዎችን አስመርቋል።
የዕለቱ ተመራቂዎች በመመረቃቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፤ ማህበረሰባቸውን በትጋት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ አማሮ አርሳባ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
More Stories
በ2018 የትምህርት ዘመን ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዲመጡ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረዉ መቀጠል ይኖርባቸዋል – የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻዉ ከበደ
ተማሪዎች በወቅቱ ትምህርት ቤት ቀርበዉ እንዲመዘገቡ ወላጆች የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ተናገሩ