በ2018 የትምህርት ዘመን ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዲመጡ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረዉ መቀጠል ይኖርባቸዋል – የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻዉ ከበደ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ2018 የትምህርት ዘመን ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዲመጡ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረዉ መቀጠል ይኖርባቸዋል ሲሉ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻዉ ከበደ ገለጹ።
በዞኑ ባለፉት ጊዜያት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ቀጣይነት እንዲኖራቸዉ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።
አቶ እንዳሻዉ የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ሀገር የሚጠቅም ትዉልድ እንዲፈጠር የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸዉን ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት ማህበረሰቡን በማስተባበር ባለፈዉ የትምህርት ዘመን ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የትምህርት ጥራትን የሚያስጠብቁ ድጋፎች መደረጋቸዉን ገልጸዋል።
መሰል ተግባራት በ2018 የትምህርት ዘመን ቀጣይነት እንዲኖራቸዉና ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ስለሆነም ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ በሚመለከታቸዉ አካላት የተጀሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረዉ ሊቀጥሉ ይገባቸዋል ብልዋል።
በ2018 የትምህርት ዘመን ከ3 መቶ 51 ሺ በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ ግብ ተጥሉ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ እንዳሻዉ፤ የተማሪ ወላጆች፣ መምህራን፣ በየደረጃዉ ያሉ አመራሮችና የሚመለከታቸዉ አካላት እቅዱን ከግብ ለማድረስ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
ከነሐሴ 19/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት የሚቆየዉ የተማሪዎች ምዝገባ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተጠናቆ የመማር ማስተማሩን ስራ በጊዜ ለማስጀመር ሁሉም አካላት በኃላፊነት መንቀሳቀስ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ትዕግስቱ ጴጥሮስ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
አሊያንስ ኮሌጅ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን በማፍራት የሀገሪቱን ዕድገት ለማፋጠን የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታወቀ
ተማሪዎች በወቅቱ ትምህርት ቤት ቀርበዉ እንዲመዘገቡ ወላጆች የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ተናገሩ