የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ተናገሩ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ተናገሩ፡፡
የዞኑ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 25ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
በጉባኤው ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሀድያ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ እቴነሽ ሙሉጌታ፥ በበጀት ዓመቱ በየደረጃ የሚገኙ ምክር ቤቶች ጉባኤ በማድረግ በልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙርያ ውይይት በማድረግ የህብረተሰቡ የመልማት ጥያቄ እንዲመለስ የድርሻቸውን ተወጥተዋል።
በበጀት ዓመቱ የማዳበሪያ አቅርቦት፣ የሆሳዕና ከተማ ኮሪደር ልማት፣ የተማሪዎች ውጤት፣ የሰላም ጉዳዮች እና የኦዲት ግኝት የማስመለስ ሂደት ውጤታማ እንደነበር አንስተዋል።
በ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፍ የተመዘገበው ውጤት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የምክር ቤቱ አባላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ወ/ሮ እቴነሽ ጠይቀዋል።
ምክር ቤቱ በ4ተኛ ዙር 13 ዓመት 25ኛ መደበኛ ጉባኤ የሀድያ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማድመጥ፣ የምክር ቤቱ የ2018 በጀት ላይ ውይይት ማድረግ፣ የሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት እቅድ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅና ሌሌች አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል ።
ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 13ኛ ዓመት 25ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ዘጋቢ: ጌታቸው መጮሮ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
ተማሪዎች በወቅቱ ትምህርት ቤት ቀርበዉ እንዲመዘገቡ ወላጆች የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
በሆሳዕና ከተማ እየተገነባ ያለውን የመንገድና የኮሪደር ልማት ስራ በታቀደው ጊዜ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ለተማሪዎች ምዝገባ ውጤታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንዳለባቸው የቀቤና ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አሰታወቀ