በሆሳዕና ከተማ እየተገነባ ያለውን የመንገድና የኮሪደር ልማት ስራ በታቀደው ጊዜ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሆሳዕና ከተማ እየተገነባ ያለውን የመንገድና የኮሪደር ልማት ስራ በታቀደው ጊዜ በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ለነዋሪዎችና እንግዶች ምቹ ለማድረግ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት አስታወቀ።

የመንገድና የኮሪደር ልማት ስራዎች ለነዋሪዎች ምቹ አከባቢ ከመፍጠር በሻገር የከተማውን ገጽታ እየቀየረ ስለመምጣቱ አንዳንድ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አንስተዋል።

በከተማው ያገኘናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በመንግሥትና በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ከተማውን ለዜጎች ምቹ በማድረግ ረገድ ተስፋ የሚጣልበት መሆኑን አንስተው ከጊዜ ወደ ጊዜ ገጽታውንም በፍጥነት እየቀየረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም የእግረኛና የተሽከርካሪ መንገድ ያለተመቻቸ በመሆኑ የትራፊክ መጨነቅ አደጋዎች የመከሰት አጋጣሚዎች በስፋት እንደነበሩ አንስተው አሁን ላይ በተዋበ አከባቢ ሰዎች እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱ እንዳስቻላቸው አስረድተዋል።

ሌላኛዋ በከተማ ሲንቀሳቀሱ ያገኘናቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ ሙሉነሽ ላሞሬ በበኩላቸው በከተማው እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደርና የተለያዩ የልማት ስራዎች ህዝቡ በተለያዩ ወቅት ያነሳቸው የነበሩ የልማትና የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ጥያቄዎችን ከመመለስ ረገድ ከፍተኛ ጠቃሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

በመሆኑም በከፍተኛ ወጪ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች እስኪጠናቀቁ ህብረተሰቡ በባለቤትነት መንከባከብ መጠበቅና ስራው ከግብ እስኪደርስ የድርሻውን መውጣት እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎቹ አሳስበዋል ።

በከተማው እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደርና ሌሎች የግንባታ ስራዎች በተለይም በዋናው አስፋልት መንገድ የህንፃዎች፣ የአጥርና የኮሪደር ስራዎች በተቀመጠው ደረጃ መሠረት ተጣጥመው እንዲሰሩ እየተደረገ ይገኛል ያሉት በከተማው ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ም/ስራ አስኪያጅና የኮንስትራክሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማኑኤል ደመቀ ናቸው።

የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ም/ስራ አስኪያጅና የቤቶች ዘርፍ ኃላፊና የኮርደር ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ኢያሱ ግርማ በበኩላቸው፥ በከተማው ተጠናክሮ የቀጠለው የኮሪደርና የመንገድ ልማት ስራ ከተማው ለኑሮ፣ ለንግድ ምቹ፣ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንድትሆን እንደሚያግዛት አንስተው በቅርቡ የስራው አካል የሆነው 10 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ እየተገነባ ይገኛል ብለዋል።

የመንገዱ ስራ ከአምቢቾ እስከ ሻፊ ማዞርያ ድርስ ያለውን እንደሚያከትት ጠቁመው ስፋቱ 36 ሜትር የሆነ የተሽከርካሪ፣ የእግረኛ የብስክሌት ደረጃውን የጠበቀ የጎርፍ ማፈሰሻ እና ግሪኔሪ እንደሚያካት ተናግረዋል ።

የከተማው ህብረተሰብ በልማት ስራዎች ላይ እያደረገ የሚገኘው ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን ያውሱት አቶ ኢያሱ በከፍተኛ ወጪ በተገነቡ የኮሪደር መሠረተ ልማት ስራዎች ላይ ግንዛቤ ከመፍጠር በሻገር አስተማሪ ርምጃ መውሰዱ ስለመጀመሩ አብራርተዋል ።

የመሳይ ኦሊ የስራ ተቋራጭ ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ በበኩላቸው ድርጅቱ የረጅም ጊዜ ልምዱን በመጠቀም በጥራትና በፍጥነት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ዘጋቢ: ሄኖስ ካሳ – ከሆሳዕና ጣቢያችን