ተግዳሮቶችን ተቋቁመው ውጤታማ ለሚሆኑ ተቋማትና ፈፃሚዎች ዕውቅና መስጠት የውድድር መንፈስ ለመፍጠርና የተሻለ የአሰራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ያስችላል ሲል በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ አሰተዳደር አስታወቀ

ተግዳሮቶችን ተቋቁመው ውጤታማ ለሚሆኑ ተቋማትና ፈፃሚዎች ዕውቅና መስጠት የውድድር መንፈስ ለመፍጠርና የተሻለ የአሰራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ያስችላል ሲል በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ አሰተዳደር አስታወቀ

‎የወረዳው ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት የለውጥ ሥራዎችን በመተግበር የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ተቋማትና ግለሰቦችን የዕውቅናና ሽልማት መድረክ በሃና ከተማ አካሂዷል።

‎የወረዳው ስቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ደምሴ በንግግራቸው፤ በሀገራችን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ተቋም ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ የመንግስት አሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ለህዝብ አገልግሎት ተደራሽነት አይተኬ ሚና ሲጫወት መቆየቱን አስታውሰዋል።

‎ይሁን እንጅ የሪፎርምና የአሰራር ሥርዓቶችን በአግባቡ ከመተግበር አኳያ መቀዛቀዝ ይስተዋላል ያሉት ኃላፊው፤ አመራሩና ባለሙያው ለተግባራቱ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ አመላክተዋል።

‎የሳላማጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህጉ ቅጣቱ በንግግራቸው፤ ሀገርንም ሆነ ተቋምን መቀየር አይቻልም ከሚል አመለካከት በመውጣት በየተቋሞቻችን ያሉ የሥራ አፈፃፀሞቻችንን የምንፈትሽበትና ጉድለቶችን በማረም ለቀጣይ ሥራ ግብዓት የሚገኝበት መድረክ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

‎አክለውም ለሁሉም ሥራ ስኬት ቅንጅትና ትብብር ወሳኝ ነው ያሉት ኃላፊው፤ ተቋማትና ፈፃሚዎች ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ውጤታማ የሆኑትን ዕውቅና መስጠት የውድድር መንፈስና ሥርዓት እንዲዘረጋ የሚያስችል መሆኑንና በዚያው ልክ ጉድለት ያለባቸው ራሳቸውን የሚፈትሹበት ነው ሲሉ አመላክተዋል።

‎የውይይት መነሻ ሰነድ በጽህት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዘለቀ ደምሴ የቀረበ ሲሆን ከሰው ኃይል እጥረት፣ በስልጠና አቅም ከመገንባት አኳያና ከሌሎችም አንፃር የሚታዮ ችግሮች ሊፈቱ እንደሚገባ በተሳታፊዎች ተነስቷል።

‎የመድረኩ መሪዎችም ከሰው ኃይል አንፃር ያሉ ችግሮችን በቀጣይ እየለዮ የመፍታት ሥራ እንደሚሰራና የባለሙያ አቅም መገንቢያ ስልጠናና ሌሎችን ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱ ገልፀዋል።

‎ከሁሉም በላይ በባለቤትነት ሁሉም የድርሻውን ወስዶ በመሰራት የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር እንደሚያስፈልግ ኃላፊዎቹ በምላሻቸው አመላክተዋል።

‎በመድረኩ በአፈፃፀም ውጤታማ የሆኑ ተቋማትና ግለሰቦች ዕውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

‎ዕውቅናና ሽልማት ያገኙ ተቋማት እና ግለሰቦችም በሽልማቱ ደሰተኛ መሆናቸውንና በቀጣይ በተሻለ ሁኔታ የህዝብ አገልግሎት ለመሰጠት እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል።

‎ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን