ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ በኩል የምክር ቤቱ አባላት ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ
በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሣ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 32ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።
የወረዳው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አየለ አይኑ፥ ምክር ቤቱ ከፍተኛ የህዝብ ሥልጣን ባለቤት መሆኑን ተናግረው የህዝብ ሉዓላዊነት መግለጫ በመሆኑ፥ በመንግስት አሰራር ውስጥ የህዝብ ተሳትፎ የሚያረጋግጥ ተቋም ነው ብለዋል፡፡
ምክር ቤቱ የህዝብና የመንግስት ሀብትና ንብረት ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንድውል ቁጥጥርና ክትትል የሚያደርግ ተቋም እንደሆነ ገልጸው፥ በበጀት ዓመቱ የአስፈጻሚ አካላት ዕቅድ ክንውን መገምገምና ግብረ -መልስ መስጠት፣ ጉባኤ ማካሄድ፣ የኦዲት ግኝት ዕዳ አስመላሽ ግብረ-መልስ መስጠት፣ የቀበሌ ምክር ቤቶች በየምክር ቤቶቻቸው ጉባኤ ማካሄድ፣ ለህዝብ ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን እንዲወሰኑ በማድረግ የተሻለ ተግባራትን በበጀት ዓመቱ ተጠናክሮ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ አብክረው መወያየት ያለበትን ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ በኩል የምክር ቤቱ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም አፈ ጉባኤው አስገንዝበዋል።
ጉባኤው የ4ኛ ዙር 31ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣ የምክር ቤቱን 2017 ዕቅድ ክንውን ሪፖርትና የ2018 ዓ/ም ጠቋሚ ዕቅድ መርምሮ ማጽደቅ፣ የወረዳው አስፈፃሚ አካላት የ2017 ዓ/ም ክንውን ሪፓርትና የ2018 ጠቋሚ ዕቅድ መርምሮ ማጽደቅ፣ እንዲሁም 2018 ዓ/ም የበጀት አዋጅና በጀት ረቂቅ መርምሮ ማጽደቅና አዳዲስ የመንግስት ተሿሚዎች ሹመት በመስጠት ጉባዔ ለሁለት ቀን እንደሚመክር ከመርሐ ግብሩ ለማወቅ ተችሎል ።
ዘጋቢ፡ አሸናፊ ግዛው – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
አሊያንስ ኮሌጅ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን በማፍራት የሀገሪቱን ዕድገት ለማፋጠን የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታወቀ
በ2018 የትምህርት ዘመን ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዲመጡ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረዉ መቀጠል ይኖርባቸዋል – የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻዉ ከበደ
ተማሪዎች በወቅቱ ትምህርት ቤት ቀርበዉ እንዲመዘገቡ ወላጆች የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ