የትራፊክ አደጋን ከመቀነስና ከመከላከል አኳያ አሽከርካሪዎችና እግረኞች የትራፊክ ህግና- ደንብን መከተልና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

የትራፊክ አደጋን ከመቀነስና ከመከላከል አኳያ አሽከርካሪዎችና እግረኞች የትራፊክ ህግና- ደንብን መከተልና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የትራፊክ አደጋን ከመቀነስና ከመከላከል አኳያ አሽከርካሪዎችና እግረኞች የትራፊክ ህግና- ደንብን መከተልና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የአ/ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችና አሽከርካሪዎች አሳሰቡ፡፡

‎አሽከርካሪዎች በተለይም ለእግረኞች ቅድሚያ በመስጠትና የተወሰነውን የፍጥነት ወሰን መጠበቅ እንደሚገባቸው የከተማው ትራፊክ ፍሰት ቁጥጥርና የአደጋ መከላከል ማስተባበሪያ አስታውቋል፡፡

‎አስተያየታቸውን የሰጠን የከተማው ነዋሪዎች እግረኞች የግራ ጠርዝን ይዞ ከመጓዝ አኳያና በመንገዶች ላይ በእግረኞች ማቋረጫዎችን ተጠቅሞ በመሻገር የትራፊክ አደጋን መከላከል እንደሚቻል አመላክቷል፡፡

‎አሽከርካሪዎች የተሸከርካሪዎችን አመታዊ እድሳቶችንና የቴክንክ ምርመራዎችን በማድረግ በተለይም እግረኞች በብዛት በሚኖሩባት መሻገሪያዎች ላይ ለእግረኞች ቅዲሚያ መስጠት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

‎ምክትል ኢንስፔክተር ብዙነሽ አመኑ የአ/ምንጭ ከተማ የትራፊክ አደጋ የግንዛቤ ማስጨበጫ ቡድን መሪ ሲሆኑ አደጋን ቀንሶ ከማሽከርከር አኳያ ለአሽከርካሪዎችና ለእግረኞች ሰፊ ግንዛቤ እየሰጠ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

‎በ2017 በጀት አመት በከተማው የትራፊክ አደጋን ለመከላከልና ለመቀነስ በርካታ ተግባራት መስራታቸውን ምክትል ኮማንደር አዲሳለም እስራኤል የአ/ምንጭ ከተማ ፖሊስ ትራፊክ ፍሰት ቁጥጥርና አደጋ መከላከል ማስተባበሪያ ኃላፊ አስረድተዋል፡፡

‎ዘጋቢ፡ ስምረት አስማማው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን