ክልሉን የሠላም ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ክልሉን የሠላም ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ አቶ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ አሳሰቡ።
የክልሉ ፀጥታ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት 3ኛ ዙር መደበኛ ጉባኤውን በአ/ምንጭ ከተማ አካሂዷል ።
በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ዉስጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ከፀጥታው አካላት ጋር በጋራ በመስራት ክልሉን የሠላም ተምሳሌት ለማድረግ የተሠራው ሥራ አበረታች መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ አቶ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለፁ።
በቀጣይም የተጀመረውን የሠላምና የአንድነት ተምሳሌትነት ለማስቀጠልና በ2018 ዓ.ም የታቀዱ ሀገራዊና ክልላዊ አጀንዳዎችን በሠላም እንዲጠናቀቁ በቅንጅት መሰራት እንዳለበትም ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ አሳሰበዋል።
የጸጥታ አካሉን ለማጠናከር የውስጥ አቅሞችን መጠቀም እንደሚገባ ያሳሰቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የጸጥታ አካሉ እና አመራሩ ሠላምን በሠላም ጊዜ መሥራት እንዳለበትም መክረዋል።
በጉባኤው ከክልሉ ሁሉም ዞኖች ሪጂዮ ፖሊ ከተሞች፣ ከፌደራል ፖሊስ እና ክልሉ ጸጥታ አባላት ተሳትፈውበታል።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የግል ጤና ተቋማት ሙያዊ ስነምግባራቸውን ጠብቀው ተገቢ ግልጋሎት መስጠት እንደሚጠበቅባቸው ተጠቆመ
የጉራጊኛ ቋንቋ የስራ፣ የትምህርትና የሚዲያ ቋንቋ እንዲሆን በተላለፈው ውሳኔ መደሰታቸውን የእዣ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ
አሊያንስ ኮሌጅ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን በማፍራት የሀገሪቱን ዕድገት ለማፋጠን የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታወቀ