ህዝበ ሙስሊሙ ከአካባቢ አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ አንድነትና ሠላም እንዲረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝ የኣሪ ዞን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ገለፀ
ምክር ቤቱ በኡለማ ወይም በኃይማኖቱ ሊቃውንት፣ በምሁራን፣ በወጣቶች፣ በሴቶችና በሥራ ማህብረሰብ ዘርፍ በቀጣይ ለአምስት ዓመት የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን የሚመሩ አካላትን ምርጫ ባካሄደበት ወቅት ነው ይህንን የገለፀው።
የኣሪ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱልቃድር አሊ እንደገለፁት፤ የተመረጡ አካላት የመላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች አንድነትንና ሠላምን አጥብቀው የሚሠሩ እንዲሁም ከሌሎች ቤተ እምነቶችም ጋር በመተባበር ከአካባቢ አልፎ ለሀገር መንግስት ሠላምና አንድነት ኃላፊነታቸውን ሊውጡ ይገባል።
የተካሄደው ምርጫም ሰላማዊ፣ ሁሉን ያሳተፈ፣ በግልፀኝነት የተካሄደ ነበር ሲሉም መራጮችና ምርጫውን ያስተባበሩ አካላት ተናግረዋል።
ምርጫው ከከተማ አስተዳደር ወይም ወረዳ ጀምሮ እስከ ፌደራል ድረስ በየደረጃው እየተካሄደ ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ድረስ በተመሳሳይ መልኩ እንደሚጠናቀቅ ሰብሳቢው ገልፀዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የስራ ዘመን 19ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
የሀድያ የልማት እድገት፣ አንድነትና የመተባበር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 12ተኛ ዓመት 5ተኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው