የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የስራ ዘመን 19ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
ሀዋሳ፣ ነሐሴ 10/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የስራ ዘመን 19ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በዞኑ ዋና አፈጉባኤ አቶ መሀመድአሚን ሀጂ ማሕዲ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት በስራ ዘመኑ በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤት አባላት በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰሩ የሚገኙ ልማቶችን በመከታተል እና ግብር መልስ መስጠት በመቻሉ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
በግብርና ግብዓት አጠቃቀም እና አመላለስ ተግባር በርካታ ስራዎችም ተሰርተው ውጤትመመዝገቡን የገለጹት አፈ ጉባኤው የዞኑን ውስን የመንግስት ሀብት በመጠቀም የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለማልማት የግብር አሰባሰብ ተግባር ስራ በተጠናከረ መልኩ መሠራቱን ጠቅሰዋል።
በከተማ ደረጃም የቁሊቶን ከተማ ውብት ለማስጠበቅ የኮሪዳር ልማት ስራ እየተሰራ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
የሀላባ ዞን የቁሊቶ ከተማ አለም አቀፍ የስተዲየም ግንባታ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ትኩራት ተሰጥቶበት እየተሰራ በመሆኑ እና በሀገር እና ከሀገር ውጪ ገቢ የማሰባሰብ ተግብር ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው አቶ መሀመድአሚን ሀጂ መሐዲ የገለጹት።
በጉኤው የ2017 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2018 በጀት አመት ጠቋሚ እቅድና ረቂቅ በጀት ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዘጋቢ፡- አብድልሀፊዝ መሐመድ

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ