በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 12ተኛ ዓመት 5ተኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 12ተኛ ዓመት 5ተኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

‎ሐዋሳ፣ ነሐሴ10/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ምክር ቤቱ 4ተኛ ዙር 12ተኛ ዓመት 5ተኛ መደበኛ ጉባኤው በቆሼ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

‎የማረቆ ልዩ ወረዳ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሻምበል ደበሮ ልዩ ወረዳው የሰላምና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

‎የልዩ ወረዳው ህዝብ በሁሉም ዘርፎች ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ እየሰራን ነው ብለዋል።

‎በጉባኤው የልዩ ወረዳው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጉባኤ አጀንዳዎችን መርምሮ ማጽደቅ ፣ የአስተዳደር ጽ/ቤት፣የምክር ቤት፣የከፍተኛ ፍ/ቤት አፈጻጸሞችን ሪፖርት እና የ2018 ረቂቅ በጀትን መርምሮ ማጽደቅ የጉባኤው መርሀ ግብሮች ናቸው።

‎‎

‎የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ የ2017 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤት አባላቱ በማቅረብ ላይ ናቸው።

‎ዘጋቢ :- አብደላ በድሩ