ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ ዞን በ4 ነጥብ 3  ቢሊዮን ብር እየተገነባ ያለው የእህል ማከማቻ ዲፖ ጎበኙ

ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ ዞን በ4 ነጥብ 3  ቢሊዮን ብር እየተገነባ ያለው የእህል ማከማቻ ዲፖ ጎበኙ

ሐዋሳ፣ ነሐሴ 10/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሀድያ ተወላጅ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ ዞን በሌሞ ወረዳ ክድግሳ አከባቢ በ4 ነጥብ 3  ቢሊዮን ብር እየተገነባ ያለው የእህል ማከማቻ ዲፖ  የፌዴራል  አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን  ኮሚሽነር  አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም የተመራ ልኡክ ምልከታ አድርጓል::

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን  ኮሚሽነር  አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በዞኑ  በፌዴራል መንግስት እየተገነባ ያለው የእህል ማከማቻ ዲፖ 1 ነጥብ 8  ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እህል መያዝ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል::

የግንባታ  ስራው ወጪ በፌዴራል  መንግስት  የሚሸፍን መሆኑን  ጠቁመው 4 .3  ቢሊዮን ብር ተመድቦ  እየተሰራ መሆንም አምባሳደሩ አመላክተዋል።

ግንባታ በአሁኑ ወቅት 45  በመቶ መድረሱን የገለጹት ዶ/ር ሽፈራው እስከ ቀጣይ ዓመት ግንቦት  ወር ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በጉብኝቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፍና የመንግስት ዋና ተጠሪ  ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የፌዴራል የብልጽግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ  አቶ መለሰ ዓለሙ ፣ የኢፌዲሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ በጠቅላይ ሚነስትር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮችና የሴክተሮች ክትትል ዘርፍ  ሚኒስትር ዲኤታ  አቶ አክሊሉ ታደሰ፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ  ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ከተማ ክላስተር አስተባባሪና የኮንስትራክሽንና የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ  ወ/ሚካኤል፣ የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ ጨምሮ የፌዴራል፤ የክልልና  የዞን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች በሀድያ ዞን በሀድይ ነፈራ የተለያዩ ሀገር በቀል እና የፍራፍሬ ችግኝ ተከላ መርሃ ግር አከናውነዋል፡፡

ዘጋቢ:-በየነ ሰላሙ ከሆሳዕና  ጣቢያችን