የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 የትምህርት ዘመን የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች እና የ3ኛው ዙር “ትምህርት ለትውልድ” ማስጀመሪያ መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው
የማስጀመሪያ መድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በዚሁ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ የ2017 የትምህርት ዘመን የክረምት ወራት ስራዎች እና የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማትና ግብዓት ለማሟላት የተዘጋጀ “የትምህርት ለትውልድ” የንቅናቄ ዕቅድ ይቀርባል።
በተጨማሪም የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም አተገባበር፣ የተመዘገቡ ውጤቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም በሴቭ ዘ ችልድረን የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።
በመድረኩ ከክልል እስከ ወረዳ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ