ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል በየጊዜው ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባው ተገለፀ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሣላማጎ ወረዳ የወጣቶች ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሃና ከተማ ተካሂዷል።
በአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ላይ የተገኙት የሣላማጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህጉ ቅጣቱ፤ ስፖርት ጤናማ ትውልድ በመቅርጽ በኩል ጉልህ ሚና እንዳለው አንስተው ተላለፈ ካልሆኑ በሽታዎች ማለትም ከስኳር በሽታ፣ ከደምግፊትና ከአላሰፋላጊ ውፍረት እራስን ለመከላከል ሁሉም ማህበረሰብ በየጊዜ እየወጣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያድርግ አሳስበዋል፡፡
በአካል ብቃት ስፖርት እንቅስቃሴ ከተሳተፉ የከተማው ነዋሪዎች መካከል ወ/ሮ አበባ ሎችኮሮ፣ አቶ ግራኝ አስፋውና ሌሎችም ስፖርት ጤናማ ትውልድ ከመቅርጽ በሻገር ለአካል ብቃትና ለአእምሮ እድገት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠረት አስፋው እንደገለፁት፤ በየጊዜው የአካል ብቃት ስፖርትን በመስራት ጤናማ የሆነ ትውልድ ለመፈጠር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ውሳኑ ዶይዴ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ስፖርታዊ ውድድሮች ማህበረሰብን ከማቀራረብ ባሻገር ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ስለሚያስችሉ ሊጠናከሩ እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል
ክሪስታል ፓላስ የኮሙዩኒቲ ሽልድ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ
ኬሮድ የስፖርትና ልማት ማህበር ተተኪ አትሌቶች የሚፈሩበትና ለሀገራችን የአትሌቲክስ ዘርፍ ማደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ የስፖርት ማህበር መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ