ክሪስታል ፓላስ የኮሙዩኒቲ ሽልድ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

ክሪስታል ፓላስ የኮሙዩኒቲ ሽልድ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

ሀዋሳ: ነሐሴ 04/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ክሪስታል ፓላስ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊቨርፑልን በመለያ ምት በማሸነፍ የኮሙዩኒቲ ሽልድ ዋንጫን አሸናፊ ሆኗል።

ከፍተኛ ፉክክር በታየበትና በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ሊቨርፑልን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል።

ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ባደረጉት ፍልሚያ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ሲያጠናቅቁ÷ የሊቨርፑልን ግቦች አዲስ ፈራሚዎቹ ሁጎ ኢኪቴኪ እና ጀረሚ ፍሪምፖንግ አስቆጥረዋል፡፡

የክሪስታል ፓላስን ሁለቱን ግቦች ማቴታ እና ኢስማኢል ሳር አስቆጥረዋል።

ጨዋታው በሁት አቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት ያመሩት ቡድኖች ክሪስታል ፓላስ በመለያ ምት ሊቨርፑልን 3 ለ 2 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።