የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡

በዚህም መሠረት፦

1ኛ.የ2018 በጀት አመት የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎች ዙሪያ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል።

2ኛ. በ90 ቀናት ዕቅድ ውስጥ የተካተቱ የካፒታል ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ አቅጣጫ አስቀምጧል።

3ኛ. የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎች ዙሪያም ምክር ቤቱ የተወያየ ሲሆን ለተግባሩ ውጤታማነት ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ አቅጣጫ ተቀምጧል።