የሴቶች የትምህርት ተሳትፎ ካለፉት ዓመታት ይልቅ አሁን እያደገ መምጣቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ

የሴቶች የትምህርት ተሳትፎ ካለፉት ዓመታት ይልቅ አሁን እያደገ መምጣቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ

የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተና መቁረጫ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2017 የትምህርት ዘመኑ የ8ኛ ማጠናቀቂያ ፈተና ከተፈተኑ 36 ሺህ 683 ተማሪዎች መካከል 50 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች መደበኛ 59 ከመቶ ወደ ቀጣይ ክፍል ማለፍ መቻላቸው ተገልጿል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በላቀ ደረጃ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እንዲቻል ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ የተጠናከረ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

በመሆኑም የመምህራን አቅምን የማሣደግ፣ የትምህርት ግብኣት የማሟላትና የፈተና አስተዳደር ሥርዓት ከስርቆትና ከኩረጃ በጸዳ መልኩ የማከናወን ሥራዎችም ተሠርተዋል።

በመሆኑም በ2017 የትምህርት ዘመን መደበኛ ተማሪ 59.13 ከመቶ 50 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ከግል ማለትም በርቀት እና በማታ ከተፈተኑት መካከል ደግሞ 33.4 የሚሆኑት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማስመዝገብ መቻላቸውን ገልጸዋል።

የ8ኛ ክፍል መደበኛ ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ፣ አርብቶ አደር አካባቢ ተማሪዎች እና የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ያላቸው ተማሪዎች ማለፊያ ነጥባቸው 46 እና ከዚያ በላይ ማምጣት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን 36 ሺህ 683 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት ሲከታተሉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 20 ሺህ 7 መቶ 44 ተማሪዎች 50 እና ከዚያ በላይ ማምጣት መቻላቸውንም አስረድተዋል።፡

በ2017 የትምህርት ዘመን ከዳዉሮ ገሣ ተማሪ አቤኔዘር መርክኔ መንገሻ 98.57 በማምጣት የላቀ ውጤት አስመዝግቧል።

ከአምናው ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር የ14 ከመቶ ጭማሪ መሻሻል መኖሩንም አስረድተዋል።

በ2018 የትምህርት ዘመን ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን በራስ አገዝ የምገባ ሂደት ምገባ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

ከ50 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ የትምህርት ግብኣት በጎ ፈቃደኞችን በማሣተፍ እየተካሄደ እንዳለም አስረድተዋል።

ትውልድን ለመጪው ዘመን ለማዘጋጀት እንዲቻል ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ትምህርት ለትውልድ በሚል መሪ ቃል እንደሚሰበሰብም በመግለፅ።

በ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተና የሴቶች ውጤት ከወንዶች እጅግ የተሻለ በመሆኑ የማለፊያ ውጤት በተመሣሣይ 50 ከመቶ መደረጉንም ተናግረዋል።

የ2018 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ከነሐሴ 19/2017 ጀምሮ የሚካሄድ በመሆኑ ለስኬቱ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ተማሪዎችም sw.ministry.et በኢንተርኔት መረብ ስማቸውንና የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ማየት እንደሚችሉም ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡ መሣይ መሠለ – ከዋካ ጣቢያችን