የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግና አካታች በሆኑ እቅዶች መመራት እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግና አካታች በሆኑ እቅዶች መመራት እንደሚገባ በካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ረዳት የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ጽዮን ታዬ ገለጹ።
ኃላፊዋ ይህንን የገለጹት የፓርቲውን የ2018 በጀት ዓመት የተግባር ዕቅድ ባቀረቡበት መድረክ ነው።
በአመራሮችና በአባላቱ ዘንድ የብልጽግናን እሳቤ በማስረጽና የአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ በማተኮር የፓርቲውን አደረጃጀት ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።
ሀገር-አቀፍና ዓለም-አቀፍ ነባራዊ ሁኔታዎችን በመገንዘብና በእውቀት ላይ የተመሠረተ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት ተግባራትን መከወን አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተቀመጡ የውሳኔ አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ የመልካም አስተዳደር ስራዎች በህዝብ ተሳትፎ እንዲጎለብቱ ይሰራል ብለዋል።
የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ አካታች፣ አሳታፊ እና ሁሉን-አቀፍ በሆኑ ግልጽ እቅዶች መመራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ ትዕግስቱ ጴጥሮስ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ብሔረሰብ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት “ኦገት” ለዘመናዊ የፍትህ ስርዓት ያለው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
ከ1 መቶ ሺህ በላይ መራጮች የ2017 የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምርጫ እንደሚሳተፉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ገለጸ
የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የገቢ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቆመ