የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ በጀሙ ከተማ እያካሄደ ይገኛል

የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ በጀሙ ከተማ እያካሄደ ይገኛል

‎ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዞኑ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ቢልልኝ ወልደሰንበት እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ በመሆናቸው የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ሚናዎችን እየተወጡ ይገኛሉ።

‎በበጀት ዓመቱ ያለአግባብ የባከኑ የመንግስት ሀብትና ንብረት እንዲመለሱ እና የአሰራር ጥሰቶች እንዲታረሙ በተሰራው ስራ አመርቂ ውጤት በመመዝገቡ በቀጣይም ልዩ ትኩረት በመስጠት ይሰራል ብለዋል።

‎ዋና አፈ ጉባኤው አክለውም በሀገራችን የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ምክር ቤቱ ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሮአዊ ችግሮችን በመቅረፍ ስኬታማ እንዲሆን ሊረባረቡ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

‎ምክር ቤቱ በ2 ቀን ውሎው የ3ቱም የመንግስት አካላት የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም፣ የ2018 ጠቋሚ ዕቅድ እና የ2018 የዞኑ በጀት ቀርቦ እንደሚፀድቅ እንዲሁም የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር እና የሹመት ስነ-ስርዓት እንደሚካሄድ ከመርሀ ግብሩ ለማውቅ ተችሏል።

‎በዞኑ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

ዘጋቢ፡ ዮናስ ወ/ገብርኤል – ከሚዛን ጣቢያችን