የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ

የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 05/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክረምት ወራት የውክልና ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸው ‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክርቤት ገለፀ፡፡

‎የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከመረጣቸው ህዝብ ጋር በቀጣይ መወያየት እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል።

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክርቤት በ2017 በጀት አመት የፓርላማ እና የክልል ምክር ቤት አባላት የክረምት ወራት ዉክልና ስራዎች ማስጀመሪያ ምክክርና የኦሬንተሽን መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

‎መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክርቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባዉዲ በልማት የመልካም አስተዳደር የሚነሱ ጥያቄዎችን በማጤን ምላሾችን በመስጠት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል ።

‎የህዝቡን ጥያቄ በማዳመጥ ተገቢውን ምላሽና ማብራሪያ መስጠት ቀዳሚ ተግባር እንደሆነ የገለፁት ደግሞ በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፓርላማ አባልና የልዕኩ ተወካይ አቶ መለሰ መና ናቸዉ።

‎በመድረኩም በክረምት ወራት የፓርላማ አባት ወደየክልል ምርጫ ቦታቸው ሲመለሱ የማህበረሰብ ንቅናቄዎች፣ ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን አኳያ፣ የኢኮኖሚ ልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ እና መሰል ስራዎች እንደሚደግፉ በቀረበው ሰነድ ተገልጿል ።

በ2017 በጀት አመት በክልሉ በህዝብ ለተነሱት ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾችን የርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ ዶ/ር ቦሻ ቦምቤ እያቀረቡ ይገኛሉ ።

‎በመድረኩም የፓርላማ አባላት የዞን አፈጉባኤዎች ጨምሮ አስፈፃሚ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

‎ዘጋቢ፡ ስምረት አስማማው – አርባምንጭ ጣቢያችን