ለሀገር ሠላምና ልማት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ ተግባር መጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 04/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለሀገር ሠላምና ልማት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ ተግባር መጠናከር ወሳኝ መሆኑ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ገለፀ።
በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ መሪነት ከየም ዞን የተወጣጡ የወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ቡድን አባላት የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት በወልቂጤ ከተማ እያከናወኑ ይገኛል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የወልቂጤ ከተማ ሠላም፣ ልማትና አብሮነት የተረጋገጠ ሲሆን ይህንን ይበልጥ ለማሣደግ ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በከተማው በመጀመሩ የላቀ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል ።
የዛሬው በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሁለቱን ሕዝቦች አንድነትን ከማጠናከር አልፎ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚኖሩ ሕዝቦች አንድነት፣ አብሮነትና መቻቻልን ለማጎልበት የተጀመረው ተግባር ህዝባዊ መሰረት እንዲይዝ የሚያደርግ ነው ብለዋል ።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ሀላፊ አቶ አብዱ ድንቁ በበኩላቸው የሀገራችን ብልጽግና ጉዞ እውን በማድረግ ሠላምና ዲሞክራሲ ለማስቀጠል ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የጎላ ሚና አለው ብለዋል ።
ዘጋቢ፡ አስፍር ሙህዲን – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ