የሀገራችንን ሠላምና ልማት ለማስቀጠል የበጎ ፈቃድ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ገለፀ
የወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ቡድን ከቀቤና ልዩ ወረዳ ወደ የም ዞን ሣጃ ከተማ ደርሶ ደማቅ አቀባበል ተደርጎበታል።
በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከመስፈንጠር ከፍታ ወደ ላቀ ዕምርታ በሚል መሪ ቃል በሣጃ ከተማ እና ዙሪያው ፅዳት ችግኝ ተከላና ለአቅመ ደካሞች ልዩልዩ ቁሣቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
የሳጃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጌታሁን ካሣሁን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የሳጃ ከተማ ሠላም፣ ልማትና አብሮነቷ የተረጋገጠ ሲሆን ይህንን ይበልጥ ለማሣደግ ድምበር ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በከተማው በመጀመሩ የላቀ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል።
የዛሬው በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሁለቱን ሕዝቦች አንድነትን ከማጠናከር አልፎ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚኖሩ ሕዝቦች አንድነት፣ አብሮነትና መቻቻልን በመፍጠር የተጀመረው መልካም ተግባር ህዝባዊ መሰረት እንዲይዝ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በረከት ከድር በበኩላቸው፤ የሀገራችንን ብልጽግና ጉዞ እውን በማድረግ ሠላምና ዲሞክራሲ ለማስቀጠል ወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የጎላ ሚና አለው ነው ያሉት።
በክልላችን ያሉ ህዝቦች ከምንለያይበት ይልቅ የምንቀራረብበት ጉዳይ የሚበልጥ በመሆኑ በጎ ፈቃደኞች የሠላም አምባሣደር በመሆን የጋራ እሴት ማልማት ላይ ማትኮር አለባቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞን ለማሣካት መመከት መትጋት እና ማጥራት መሪ መከተል አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት እየተመራ ያለው 2ኛ ዙር ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት አምናና ዘንድሮ በሣጃ ከተማ በመጀመራችን ደስተኛ ነኝ ያሉት ደግሞ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ድንቁ ናቸው።
የወሠን ተሻጋሪ ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሀገራችን ብሎም ክልላችን የብዝሃ ብሔር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ባለቤት በመሆኑ የእርስ በርስ ትስስርን፣ መረዳዳትንና መተሳሰብን በመፍጠር አንድነታችንን ያጠናክራል ብለዋል።
የየም ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ በላይነህ ገረመው፤ በጎነት ለሀገር ዕድገት የሕዝቦች አብሮነትና ትስስር በማጎልበት ገዢ ትርክትን ለማፅረስ የሚያገለግል ትልቅ ሥራ ነው ብለዋል።
የየም ዞን ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ልደቱ ወልደ መዲን በበኩሉ፤ ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰዎች ለሰዎች የሚያደርጉት መልካም ተግባር በመሆኑ በገንዘብ፣ በጉልበትና በሀሣብ በመደጋገፍ የተቸገሩትን በመርዳት ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
በጎነት ዘር፣ ሃይማኖት፣ ጾታ እና ቋንቋ ሣይገድብ ሰው በመሆን ብቻ የሚደረግ ተግባር ስለሆነ የድርሻችንን በመወጣት መልካምነትን ማስረፅ ተገቢ መሆኑን አስረድቷል።
ተግባሩ ላይ የተሣተፉ አካላትም በጎነት ለራስ በመሆኑ ደስተኞች መሆናቸውንና ተግባሩን በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ማሙዬ ፊጣ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ለሀገር ሠላምና ልማት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ ተግባር መጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
ማረሚያ ቤቶች ከማረምና ማነፅ ሥራዎች በተጨማሪ የልማት ሥራዎችን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ገለፀ
ተመራቂ ተማሪዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ያላቸዉን እዉቀትና ክህሎት ተጠቅመዉ ዘመኑን የሚመጥን ስራ በመስራትና ተወዳዳሪ በመሆን ሀገራዊ ሀላፊነታቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ ተገለፀ