‎ተመራቂ ተማሪዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ያላቸዉን እዉቀትና ክህሎት ተጠቅመዉ ዘመኑን የሚመጥን ስራ በመስራትና ተወዳዳሪ በመሆን ሀገራዊ ሀላፊነታቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ ተገለፀ

‎ተመራቂ ተማሪዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ያላቸዉን እዉቀትና ክህሎት ተጠቅመዉ ዘመኑን የሚመጥን ስራ በመስራትና ተወዳዳሪ በመሆን ሀገራዊ ሀላፊነታቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ ተገለፀ

‎በአሪ ዞን የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸዉን 250 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ሃላፊ አቶ በዛብህ ገበየሁ፤ የቴክኒካና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ወጣቱ ትዉልድ በክህሎትና በእዉቀት፣ በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ ለሀገር እድገትና ብልፅግና አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ ብቁ ዜጋ የሚያፈራ በመሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ያላቸዉን እዉቀትና ክህሎት በማስፋት ዘመኑን የሚመጥን ስራ በመስራትና ተወዳዳሪ በመሆን ሀገራዊ ሀላፊነታቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ አሳስበዋል፡፡

‎የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብርሀም አታ በበኩላቸዉ፤ ኮሌጁ ከትምህርትና ስልጠና ባሻገር በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፍ ማህበረሰቡን በማገዝ ረገድ ትልቅ ሀላፊነት እየተወጣ መሆኑን ጠቁመዉ፤ ተመራቂ ተማሪዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ለማህበረሰቡ እና ለሀገር የሚጠቅም ችግር ፈች የሆኑ ስራዎችን መስራት እንዳለባቸዉ ተናግረዋል፡፡
‎የአሪ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ተክሌ፤ ተመራቂ ተማሪዎች ብቁና ስራ ፈጣሪ በመሆን ወቅቱን የሚመጥን ስራ በመስራት ተወዳዳሪ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

‎የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ካሳሁን ጌታቸው፤ ኮሌጁ ለ22ኛ ጊዜ በተለያዩ የስልጠና ዘርፎችና በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ትምርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሰረት ያሰለጠናቸውን 250 ሰልጣኞችን በ7 የስልጠና መስኮች በደረጃ 2 እና በደረጃ 4 ማስመረቁን ተናግረዋል፡፡

‎ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል በክሮፕ ፕሮዳክሽን የዋንጫና የሜዳልያ ተሸላሚ የሆኑ ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ስራ ጠባቂ ከመሆን ስራ ፈጣሪ ሆነው ማህበረሰባቸውን እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል።

‎ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን