ትምህርት ለሁሉም የልማት ስራዎች ትልቅ አቅም በመሆኑ የትምህርት ስብራትን በመጠገን ተወዳዳሪ የሆነ ትዉልድ ለማፍራት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ ሚና እንዳለዉ ተገለፀ
የአሪ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣ የ2018 ጠቋሚ እቅድና የክረምት ስራዎች ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡
የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ እንደገለፁት፤ ትምህርት ለሁሉም የልማት ስራዎች ትልቅ አቅም በመሆኑ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በዞኑ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች መሻሻሎች ቢኖሩም ለተማሪዎች ጊዜዉን የሚመጥን ትምህርት በመስጠት ተወዳዳሪ ከማድረግ አኳያ ያሉ የጥራት ችግሮችን ለመቅረፍ ቅንጅታዊ ስራ መሰራት ይገባል፡፡
አክለዉም ህፃናት አካባቢያቸዉንና ባህላቸዉን ጠንቅቀው እንዲያዉቁ የአራፍ ቋንቋ ትምህርትን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተደራሽ ለማድረግ የተጀመረዉ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የአሪ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ እልፊዮስ ባድሜ በበኩላቸዉ፤ ትምህርት ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳዉ የጎላ በመሆኑ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የትምህርት ግበዓትን ለሟሟላት እና መምህራንና ተማሪዎችን በትምህርት ገበታ ላይ እንዲቆዩና የተማሪ መጠነ መቅረትና መጠና ማቋረጥን ለመቀነስ ማህበረሰቡን በማሳተፍ የምገባ ፕሮግራም ለማመቻቸት የትምህርት ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት ሰጥተዉ መስራት አለባቸዉ ብለዋል፡፡
የጂንካ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዉባለም ገዛኸኝ፤ የገሊላ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የትምህርት ቤት መሻሻል የስራ ሂደት አስተዳዳሪ አቶ ተሾመ ፅጌ እና የወባ አሪ ወረዳ መምህራን ልማት አስፈፃሚ ወ/ሮ ትሁን ቸኮል በ2017 በጀት ዓመት የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ የተሻለ አፈፀፀም ለማስመዝገብ ምቹ የመማር ማስተማር ከባቢን መፍጠርና የትምህርት ግበዓትን በማሟላት ተማሪዎች ጥራት ያለዉ ትምህርት እንዲያገኙ ለመምህራን በተለያየ መልኩ ስልጠናዎችን በመስጠት የትምህርት ስብራትን ለመጠገን እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የትምህርት ብክነትና የተማሪዎች መጠነ ማቋረጥን ለማስቀረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ አሳሰቡ
የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2018 በጀት ከ1.9 ቢልዮን ብር በላይ አጸደቀ
የተፈጥሮ መስህቦችን ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሸካ ዞን አስተዳደር አስታወቀ